Gafat Endowment

ጋፋት ኢንዶውመንት  ጥር 22 ቀን 2000 ዓ.ም በክልሉ ፍትህ ቢሮ ምዝገባና ህጋዊ እዉቅና አግኝቶ ሲንቀሳቀስ የቆየና በሂደትም በበጎ አድራጎት ድርጅቶች ማህበራት መመዝገቢያና ማስተዳደሪያ አዋጅ ቁጥር 194/2004 ተመዝግቦ የሚገኝ  መንግስታዊ ያልሆነ ዘላቂ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነዉ፡፡  

The Endowment is established on January 31, 2008 and operating under Proclamation No. 194/2012 of the Amhara National Regional Government for the Registration and Management of Charitable Organizations and Associations. Gafat Endowment is a sustainable charity organization and has got its name from a special place called Gafat, where the Sebastopol Cannon was built, which was the beginning of a new technology in Ethiopia and reflects the vision of Emperor Tewodros.

ጋፋት ኢንዶዉመንትን በማቋቋም ሒደት ዋናዉንና ግንባር ቀደሙን ሚና የተጫወተዉ የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ-ኢትዮጵያ) ነዉ፡፡ አመልድ የአለም አቀፍ ተሞክሮዎችን መነሻ በማድረግ ጋፋት ኢንዶዉመንትን ለማቋቋም ሲያስብ ዋነኛ መነሻዉ የአማራ ክልል ህዝብን ከድህነትና ኋላቀርነት ለማላቀቅ በሚደረገዉ ርብርብ ዉስጥ አመልድ በዉጭ የበጀት ድጋፍ ብቻ ጥገኛ ከመሆን ተላቆ በሂደት የልማት ፕሮግራሞቹን በሀገር ዉስጥ የፋይናንስ አቅም ለማስኬድ የሚያሰችለዉን ዓላማ አንግቦ ነዉ፡፡ 

ኢንዶውመንቱ ከተቋቋመበት ጥር  2000 ዓ.ም ጀምሮ በተጓዘባቸው ዓመታት ለክልሉ ህዝብ በርካታ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀሜታዎችን በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡  ኢንዶዉመንቱ ሲቋቋም ከኢንቨስትመንትም ሆነ ከለጋሽ አካላት የሚያገኘውን ሀብት በክልሉ ውስጥ ክፍተት በሚታይባቸውና የግሉ ዘርፍ በበቂ ሁኔታ ባላለማቸው ዘርፎች ላይ ሀብቱን በማዋል በክልሉ ውስጥ ኢንቨስትመንትን የማስፋፋት፣ የሥራ እድል የመፍጠርና  የቴክኖሎጅ ሽግግር የማምጣት እና የማህበራዊ ልማትን (በጎ አድራጎት) ማስፋፋት ተልዕኮን አንግቦ ነው፡፡ ኢንዶዉመንቱ እ.ኤ.አ በ2008 ሲቋቋም ከነበረዉ አንድ ኩባንያ በመነሳት በሂደት ሶስት የኮንስትራክሽን ኩባንያዎችን በማቋቋም ዛሬ ላይ የአራት ገቢ ማስገኛ ኩባንያዎች ባለቤት መሆን ችሏል፡፡ ጋፋት ኢንዶውመንት ተልዕኮውን ለማሳካት ተቋማዊ ልህቀት፣ ኢንቨስትመንት ተኮር ሀብት ፈጠራ እና ማህበራዊ ልማት የትኩረት መስኮችን ቀርፆ ግቦችን ለማሳካት በትጋት እየሰራ ይገኛል፡፡ 

Subsidiary Companies

ኢንዶዉመንቱ በክልሉ ለሚያከናውነው የበጎ አድራጎት ተግባር ኃብት ለማመንጨት በአሁኑ ወቅት በስራ ላይ የሚገኙ አራት ኩባንያዎችን ማለትም፡-

Follow Us

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *