ኩባንያው ታማኝነት፣ጥራትና ቅልጥፍናን መርሁ በማድረግ በድልድይ፣በመንገድና በህንጻ ግንባታ ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን የማከራየት አገልግሎትም ይሰጣል፡፡በዚህ መርህ በመመራትም መቅደላ ኮንስትራክሽን ከተቋቋመ ጀምሮ ባለፉት ስድስት አመታት 23 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድን ጨምሮ ከ 40 የሚበልጡ የግንባታ ፕሮጀክቶችን አከናውኗል፡፡እነዚህም እያንዳንዳቸው የተቀመጠላቸውን የጥራት መስፈርት አሟልተው በመገንባታቸው ኩባንያው አንድም ለደንበኞቹ እርካታን መፍጠር ችሏል፤ሌላም ለራሱ ምስጋናና ተመራጭነትን አግኝቷል፡፡
በዚህም ለበርካቶች የስራ እድልን መፍጠር ችሏል፤ክልሉም በዘርፉ እያደረገ ያለውን ጥረት በማገዝ የዘርፉን ልማት በመደገፍ ላይ ይገኛል፡፡እነዚህም ተመራጭነታችንን ያጎሉታል፡፡
በመሆኑም በሚከተሉት የስራ ዘርፎች ማለትም፡-
- መንገድ፣
- ድልድይ እና
- ህንጻ ግንባታ እንዲሁም
- የኮንስትራክሽን ማሽነሪና ተሽከርካሪ ኪራይ ቢያስፈልግዎ
ምላሻችን ፈጣን ነው፡