ማህበራዊ ልማት
የስራ እድል የተፈጠረላቸዉ ወጣቶች
Mekdella Construction
Bridge
ማህበራዊ ልማት
የስራ እድል የተፈጠረላቸዉ ወጣቶች
Previous
Next
Tisisat Water works
ጢስ እሳት ውሀ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ጢስ እሳት ውሀ ስራዎች ኃ/የተ/ የግ/ ማህበር በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ ቁጥር 166/1952 ዓ.ም አንቀፅ 510-520 መሰረት እ.ኤ.አ ታህሳስ 2008 በጋፋት ኢንዶውመንት እና በአመልድ ኢትዮጵያ ባለቤትነት በብር አንድ ሚሊዮን ካፒታል የተቋቋመ በኮንስትራክሽን ስራ ዘርፍ የተሰማራ የጋፋት ኢንዶውመንት የገቢ ማስገኛ ኩባንያ ነው፡፡ ኩባንያው የክልሉን የገፀ-ምድርና ከርሰ ምድር ውኃ ኃብት ጥቅም ላይ ለማዋል በሚደረገው ጥረት፡
- በንጹህ መጠጥ ውኃ ግንባታ፣
- በመስኖ አውታር ግንባታ
- በጥልቅና መለስተኛ ውኃ ጉድጓድ ቁፋሮ
- በሶላር ፓምፕ ተከላ
- በጠብታ እና ርጭት መስኖ ግንባታ እንዲሁም በሌሎች የውሀ ልማት ግንባታ ስራዎች ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ ኩባንያ ነው፡፡
የመስኖ ግንባታ ፕሮጀክቶች
መስኖ ግንባታ ፕሮጀክቶች
የግብርናውን ዘርፍ የበለጠ ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የመስኖ አውታሮችን ማስፋፋትና ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም አንዱና ዋነኛው የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የአዳዲስና የጥገና መስኖ ግንባታ ፕሮጀቶች በመገንባት ላይ ነው፡፡
የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት
የህብረተሰቡን የንጹህ መጠጥ ውኃ ፍላጎት መነሻ በማድረግ ኩባንያው ወደ ዚህ የስራ መስክ ከተሰማራ ጀምሮ የተለያዩ ስኬል ያላቸውን የመጠጥ ውኃ ግንባታ ፕሮጀክቶች በማጠናቀቅ የውኃ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች ተደራሽ በመሆን የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል፡፡
ውሃ ጉድጎድ ቁፋሮ ፕሮጀክት
የከርሰ ምድር ውኃን ጥቅም ላይ ለማዋል እንዲቻል በማሰብ የሚከናወኑ የቁፋሮ ስራዎች ለንጹህ መጠጥ ውኃ፤ ለመስኖና ለኢንዱስትሪ ፓርኮች፤ ለተጣራ የማእድን ውኃ አገልግሎት የሚውሉ በመሆናቸው ስራው በተገቢው ጥናት፤ የቁፋሮ ዘዴና ቴክኖሎጂ የሚከናወን ነው፡፡
Contact Us
Location
Bahir Dar City, Atse Teodros Sub City, Near to Tedy Drivers Training center
Email:
mestesde@gmail.com
Phone:
+ 251 58 220 48 26
