Services
photo_2025-01-02_21-23-56-300x169

1.ማህበራዊ ልማት (የበጎ አድራጎት ስራዎች)፡-

  በኢንዶዉመንቱ ዓላማ ላይ የተለየ ትኩረት (Concern) የሚሰጣቸዉ የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ መሆናቸዉን በሚያረጋግጥ አግባብ እና ሁሉንም የክልሉን አካባቢዎች በፍትሃዊነት ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ ማስኬድ እንዲቻል ራሱን የቻለ የማህበራዊ ልማት (Charity) ማስፈጸሚያ መመሪያ ተዘጋጅቶና በሥራ አመራር ቦርዱ ፀድቆ ሥራ ላይ እንዲዉል ተደርጓል፡፡ ስለሆነም ኢንዶውመንቱ አመልድ-ኢትዮጵያ ቀርፆ በሚያቀርበው ፕሮጀክት አማካኝነት በማህበራዊ ተቋማት ግንባታ እና በስራ እድል ፈጠራ ላይ የበጎ አድራጎት ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

supo

2.ድጋፍና ክትትል ስራዎች፡-

 ይህ ድጋፍና የክትትል በኢንዶዉመንት ጽ/ቤቱና በኩባንያዎች መካከል የተዘረጋ ሲሆን  በሳምንት አንድ ጊዜ በዋና ዋና ተግባራት ላይ በማተኮር የኢንዶዉመንቱ አመራሮች ከኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጆች ጋር አጭር የመረጃ ልዉዉጥ የሚያካሂዱበት፣ በወር አንድ ጊዜ የጋፋት ሥራ አመራር ኮሚቴ አባላት በኩባንያ ደረጃ ወርሃዊ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ የሚያካሂዱበት፣ በሩብ ዓመት አንድ ጊዜ በጋፋት ኢንዶዉመንት ደረጃ የሁሉም የጋፋት ኩባንያዎች የእቅድ አፈፃፀም በጥልቀት የሚገመገምበት እና በመስክ የፕሮጀክቶችን አፈፃፀም በመመልከት ጥንካሬና ድክመትን ለይቶ በማውጣት የመፍትሔ አቅጣጫ የሚቀመጥበት ነው፡፡

followup

3.የአሰራር መመሪያዎችን ማፅደቅና አፈፃፀማቸውን መከታተል፡-

 በኩባንያ ደረጃ ተዘጋጅተው ወደ ኢንዶውመንት የሚመጡ የአሰራር፣የመዋቅር፣ የደመወዝና ጥቅማጥቅም ረቂቅ መመሪያዎችን ያፀድቃል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፡፡

dd

4.የአቅም ግንባታ ስራዎችን ይሰራል፡-

 የገቢ ማስገኛ ተቋማቱ ዘላቂነት ባለዉ መልኩ ተወዳዳሪና ትርፋማ ሆነዉ እንዲቀጥሉ የሚያስችል በቢዝነስ ልማትና አመራር ላይ አመለካከቱና ክህሎቱ የተገነባ ብሎም የመፈፀም አቅሙ የጎለበተ የሰዉ ኃይል ለመፍጠር የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን የመስጠትና የማስተባበር ስራዎችን ይሰራል፣

bord

5.በስራ አመራር ቦርዱ የሚሰጡ አቅጣጫዎችን ይተገብራል፡-

ኢንዶውመንቱ ዘጠኝ አባላት ባሉት የሥራ አመራር ቦርድ የሚመራ ሲሆን በተለያየ ጊዜ በሚደረጉ ግምገማዎች እና ውይይቶች የስራ አመራር ቦርዱ የሚሰጣቸውን አስተያየቶችና አቅጣጫዎች ተቀብሎ እንደ ኢንዶውመንት ተግባራዊ ያደርጋል፡፡  

DSC_0063

6. ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት ስራዎች፡-

 ኢንዶወመንቱ አሁን በስራ ላይ የሚገኙትን ኩባንያዎች የማጠናከር እና አዳዲስ የገቢ ማስገኛ ተቋማትን የማቋቋም ሒደትን በእስትራቴጅክ እቅዱ በማካተት እንደ አንድ ቁልፍ ተግባር ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡