ከስዕላዊ መረጃው እንደተገለፀው የኢንዶውመንቱን ተቋማዊ አደረጃጀት ስንመለከት ተጠሪነቱ ለቦርድ ሲሆን በዋና እና ም/ስራ አስኪያጆች የሚመራ፣ በስሩ በባለቤትነት አራት ኩባንያዎችን የሚያስተዳድርና እነዚህ ኩባንያዎች ተወዳዳሪ እና ትርፋማ ሆነው እንዲቀጥሉ ጠንካራ የሆነ የድጋፍ እና ክትትል ስርዓትን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን ኩባንያዎቹም በየጊዜው ሁለንተናዊ አቅማቸውን (holistic capacity) እያሳደጉ ትርፋማ መሆን ችለዋል፡፡