Gafat
Endowment
ጋፋት ኢንዶውመንት ጥር 22 ቀን 2000 ዓ.ም በክልሉ ፍትህ ቢሮ ምዝገባና ህጋዊ እዉቅና አግኝቶ ሲንቀሳቀስ የቆየና በሂደትም በበጎ አድራጎት ድርጅቶች ማህበራት መመዝገቢያና ማስተዳደሪያ አዋጅ ቁጥር 194/2004 ተመዝግቦ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ዘላቂ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነዉ፡፡
Gafat Endowment is a sustainable charitable organization established on January 30, 2008 by the Regional Justice Bureau in accordance with Civil Proclamation No. 165/1952 AD, Article 483 to 515. Gafat Endowment got its name from a special place called Gafat, which gives a special place in the history of technology and civilization in Ethiopia and is always remembered by generations and reflects the vision of Emperor Tewodros.
ጋፋት ኢንዶዉመንትን በማቋቋም ሒደት ዋናዉንና ግንባር ቀደሙን ሚና የተጫወተዉ የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ-ኢትዮጵያ) ነዉ፡፡ አመልድ የአለም አቀፍ ተሞክሮዎችን መነሻ በማድረግ ጋፋት ኢንዶዉመንትን ለማቋቋም ሲያስብ ዋነኛ መነሻዉ የአማራ ክልል ህዝብን ከድህነትና ኋላቀርነት ለማላቀቅ በሚደረገዉ ርብርብ ዉስጥ አመልድ በዉጭ የበጀት ድጋፍ ብቻ ጥገኛ ከመሆን ተላቆ በሂደት የልማት ፕሮግራሞቹን በሀገር ዉስጥ የፋይናንስ አቅም ለማስኬድ የሚያሰችለዉን ዓላማ አንግቦ ነዉ፡፡
ኢንዶውመንቱ ከተቋቋመበት ጥር 2000 ዓ.ም ጀምሮ በተጓዘባቸው ዓመታት ለክልሉ ህዝብ በርካታ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀሜታዎችን በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡ ኢንዶዉመንቱ ሲቋቋም ከኢንቨስትመንትም ሆነ ከለጋሽ አካላት የሚያገኘውን ሀብት በክልሉ ውስጥ ክፍተት በሚታይባቸውና የግሉ ዘርፍ በበቂ ሁኔታ ባላለማቸው ዘርፎች ላይ ሀብቱን በማዋል በክልሉ ውስጥ ኢንቨስትመንትን የማስፋፋት፣ የሥራ እድል የመፍጠርና የቴክኖሎጅ ሽግግር የማምጣት እና የማህበራዊ ልማትን (በጎ አድራጎት) ማስፋፋት ተልዕኮን አንግቦ ነው፡፡ ኢንዶዉመንቱ እ.ኤ.አ በ2008 ሲቋቋም ከነበረዉ አንድ ኩባንያ በመነሳት በሂደት ሶስት የኮንስትራክሽን ኩባንያዎችን በማቋቋም ዛሬ ላይ የአራት ገቢ ማስገኛ ኩባንያዎች ባለቤት መሆን ችሏል፡፡ ጋፋት ኢንዶውመንት ተልዕኮውን ለማሳካት ተቋማዊ ልህቀት፣ ኢንቨስትመንት ተኮር ሀብት ፈጠራ እና ማህበራዊ ልማት የትኩረት መስኮችን ቀርፆ ግቦችን ለማሳካት በትጋት እየሰራ ይገኛል፡፡
የጋፋት ኢንዶውመንት ተቋማዊ አደረጃጀት
ኢንዶዉመንቱ በክልሉ የሚያከናዉናቸዉን የበጎ አድራጎት ተግባራት ለማከናወን የሚያስችሉ በስራ ላይ የሚገኙ የገቢ ማስገኛ ኩባንያዎች ከዚህ በታች የተቀመጡት ናቸዉ፡፡
- Tana Flora
- Tisisat
- Lalibela Design
- Mekdella Construction
Tana flora which is one of amongst the four company owned by Gafat Endowment began its operations in 2008 G.C. The farm was started with one major goal, to grow and export the highest quality fresh cut roses to customers around the world. The Tana flora motto which says, “Quality, Consistency and Trust worthy to the world and responsible to the local community” is indeed true and factual as the farm in the last eight years has established itself as one of the flower exporters from Ethiopia.
ጣና ፍሎራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ተልዕኮ
- በአለም አቀፍ የአበባ ቢዝነስ ተወዳዳሪ መሆን፣
- በክልሉ ባልተነኩ የኢንቨስትመንት መስኮች በዋነኛነት በአበባ፣በአትክልትና ፍራፍሬ በመሰማራት የአከባቢውን ደህንነት በመጠበቅ፣ምርቱን ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ለውጭ ገበያ በጥናት በማቅረብ ውጤታማ በመሆን ለዜጎች የስራ እድል መፍጠር፣
- በክልሉ በአበባ፣አትክልትና ፍራፍሬ ልማት የእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማምጣት
ረዕይ
በምስራቅ አፍሪካ እ.ኤ.አ በ2025 በትርፋማነቱ ግንባር ቀደም የአበባ ቢዝነስ ኩባንያ ሆኖ ማየት
ጋፋት ኢንዶውመንት በስሩ ካቋቋማቸውና በባለቤትነት ከሚያስተዳድራቸው ኩባንያዎች አንዱ ነው፡፡ጣና ፍሎራ፡፡ኩባንያው በዋነኛነት ከፍተኛ ጥራት ያለውን አበባ በማምረት በአለም አቀፍ ደረጃ ለተጠቃሚ ለማድረስ ግብ አድርጎ በ2000 ዓ.ም የተቋቋመ ኩባንያ ነው፡፡ የጣና ፍሎራ የእርሻ ቦታ ከባህርዳር ከተማ በስተሰሜን ምእራብ በ 17 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በ124 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 40 ሄክታሩ ለአበባ ማምረቻ ውሏል፡፡በአሁኑ ወቅትም የሚከተሉትን 20 የአበባ አይነቶችን በማምረት በዋነኝነት ለውጪ ገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛል
Our mission
To construct water supply, drilling and irrigation projects with highest norms and standards and use of appropriate technology swiftly at competitive and reasonable cost to ensure customers’ satisfaction.
Our vision
In 2016 E.C Aspiring dynamic and highly qualified premier water works contractor in Ethiopia.
Our Objective
The Company has an objective to provide potable safe, adequate and reliable water to improve the livelihood of the people in Amhara Regional State.
Our Core Values
- Upholding integrity & accountability;
- Dependability & professionalism;
- Commitment to quality & innovation
Contact us at the Consulting tisisat office nearest to you or submit a business inquiry online.
looking for a first-class water work
Lalibela Study, design and supervision works Plc is one amongst the four companies owned by Gafat Endowment, was established in 2016 GC. The company is entrusted with the responsibility to contribute to the effort being made by the public sector; and is engaged mainly in the study, design, and contract administration and construction supervision of water resources, road and building projects.
ተልዕኮ
በምህንድስና ዘርፍ በመጠጥ ውሃ፣መስኖ፣ህንጻ እና መንገድ እንዲሁም በንግድና ኢንቨስትመንት የጥናት፣ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ተሳትፎውን በማሳደግ ውጤታማና በስነ-ምግባርና በክህሎት የተካነ አመራርና ሰራተኛ ሃይል በማቀናጀትና ለጋራ ራዕይ በማሰለፍ በጥራትና በብቃት የማማከር አገልግሎት በመስጠት፣ዘመናዊ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና አሰራር በጥናት፣ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች የማላመድ፤የዘርፉን ጥናትና ምርምር የመደገፍና የማበረታታት ተልጭኮ ይዞ ይሰራል፡፡
ራዕይ
በምህንድስና፣በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ በጥናት፣ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ደረጃ በጥራት እና በብቃት ተወዳዳሪና ተመራጭ ኩባንያ እ.ኤ.አ.በ2030 ተፈጥሮ ማየት፡፡
Address: www.lalibeladesign.net
የስራ ዘርፎች ማለትም፡-
- መንገድ፣
- ድልድይ እና
- ህንጻ ግንባታ እንዲሁም
- የኮንስትራክሽን ማሽነሪና ተሽከርካሪ ኪራይ ቢያስፈልግዎ
ምላሻችን ፈጣን ነው፡፡ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት አድራሻዎች ቢፈልጉን ያገኙናል፡፡
መቅደላ ኮንስትራክሽን
ስ.ቁ:-+251-582-266146/45
ፋክስ:-+251-582-266146
ድረ-ገጽ:- www.mekdellaconstruction.net
አድራሻ:- ባህር ዳር፣ ጣና ክፍለ ከተማ፣(ቀበሌ 16)